በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሴፕቴምበር 6 ይመክራሉ

ነሀሴ 27/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጪው ቅዳሜ ሴፕቴምበር 6/2025 ወይም ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚያሰባስብበት መድረክ ያካሂዳል፡፡

ኮሚሽኑ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳቸውን እያደራጁ እንዲጠብቁ ከወዲሁ ጥሪ ያቀርባል፡፡

ሰፕቴምበር 6/2025 በካናዳ ቶሮንቶ በሚካሄደው በዚህ መድረክ በአካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ከዚህ በፊት ጥሪ የደረሳችሁ ማህበራትና ተቋማት እንዲሁም በበየነ መረብ በግለሰብ ደረጃ የተመዘገባችሁ በድጋሜ የሚደረግ የማረጋገጫ ጥሪ ሳትጠብቁ በተደረገላችሁ ጥሪ መሰረት በዕለቱ እንድተገኙ ኮሚሽኑ ያሳስባል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ኮሚሽኑ በሂደቱ እንድትሳተፉ ጥሪ ካቀረበላችሁ ማህበራትና ተቋማት ውጪ ያላችሁ እና በግለሰብ ደረጃ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከታች ባለው ሊንክ በበይነመረብ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

https://forms.gle/y1kwixvgRVbdGiK99

https://www.facebook.com/EthioNDC