አምባሳደር ቴዎድሮስ ግርማ በቶሮንቶ ከተማ የሚገኝን የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የእግር ኳስ ፕሮጀክት ጎበኙ፤

አምባሳደር ቴዎድሮስ ግርማ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እግርኳስ ተጫዋች አሸናፊ ግርማ በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በአንድነት በማሰባሰብ እየሰራ ያለውን የእግር ኳስ ፕሮጀክት ጎበኙ። በጉብኝቱ ወቅት በፕሮጀክቱ ከታቀፉት ወጣት ስፖርተኞች፣ ከአሰልጣኞች እና ከስፖርተኞቹ ወላጆች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በቀጣይ ወጣቶቹን ከአገራቸው ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል ስራ በቅንጅት ለመስራት ከመግባባት ላይ ተደርሷል። በተያዘው በጀት አመት ክረምት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶች ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ እንዲሄዱ እና ከአገራቸው ጋር ያላቸው ትስስር እንዲጠነክር ለማድረግ ኤምባሲው ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህ ረገድ ታዋቂው ስፖርተኛ አሸናፊ ግርማ እንዲሁም ባልደረቦቹ እያከናወኑት ያለው ታላቅ ስራ ሊበረታታ የሚገባው እና ለሌሎችም አርኣያነት ያለው ነው ።